am_tn/luk/03/12.md

1018 B

ለመጠመቅ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዮሐንስ እነርሱን እንዲያጠምቃቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ተጨማሪ ገንዘብ አትሰብስቡ

“ተጨማሪ ገንዘብ አትጠይቁ” ወይም “ተጨማሪ ገንዘብ አትውሰዱ፡፡” ቀረጥ ሰብሳቢዎች መሰብሰብ ከነበረባቸው ገንዘብ ተጨማሪ እየሰበሰቡ ነበር፡፡ ዮሐንስ ያንን ማድረግ እንዲያቆሙ ነገራቸው፡፡

እንድትሰበስቡ ከታዘዛችሁት

ይህ የቀረጥ ሰብሳቢዎቹ ስልጣን ከሮም እንደመጣ ለማሳየት ተገብሮ/ተሳቢ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሮማውያን እንድትወስዱ ስልጣን ከሰጧችሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)