am_tn/luk/03/08.md

1.5 KiB

ለንስሀ የሚገባ ፍሬ አፍሩ

በዚህ ተለዋጭ ዘይቤ ውስጥ፣ የሰው ባህርይ ከፍሬ ጋር ተነፃፅሯል፡፡ ልክ ተክል ለተክሉ አይነት ተገቢ የሆነ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚጠበቅ ሁሉ እርሱ ንስሀ እንደገባ የሚናገር ሰው በፅድቅ እንዲኖር ይጠበቃል፡፡. አማራጭ ትርጉም፡- “ንስሀ እንደገባህ የሚያሳይ የፍሬ አይነት አፍራ“ ወይም “ከኃጢአትህ መመለሰስህን የሚያሳዩ መልካም ነገሮችን አድርግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልባችሁ መናገር

“ለራሳችሁ መናገር” ወይም “ማሰብ”

አብርሀም አባታችን አለን

“አብርሀም የእኛ የዘር ግንድ ነው” ወይም “እኛ የአብርሀም ተወላጅ ነን፡፡” ይህንን ለምን እንደሚሉ ግልፅ ካልሆነ፣ የተጠቀሰውን መረጃ ደግሞ መጨመር ትችላለህ፡- “እግዚአብሔር እኛን እንዳይቀጣን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለአብርሃም ልጆች ማስነሳት

“ለአብርሃም ልጆች መፍጠር”

ከእነዚህ ድንጋዮች

ዮሐንስ ምናልባትም በዮርዳኖስ ባህር ያሉትን ትክክለኛ ድንጋዮች እያመለከተ ነበር፡፡