am_tn/luk/03/07.md

2.0 KiB

በእርሱ ለመጠመቅ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዮሐንስ እነርሱን እንዲያጠምቃቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ የእፉኝት ልጆች

ይህ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ እዚህ ላይ “ልጆች” “የወላጆቹ ባህርይ ያለው” ማለት ነው፡፡ እፉኝቶች ክፋትን የሚወክሉ እና አደገኛ የሆኑ መርዛማ እባቦች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ክፉ መርዛማ እባቦች” ወይም “እናንተ እንደ መርዛማ እባብ ክፉ ናችሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማን አስጠነቀቃችሁ… ከሚመጣው?

እርሱ በእርግጥ መልስ እንዲሰጡ እየጠበቀ አልነበረም፡፡ ዮሐንስ ህዝቡን እየገሰፀ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዳይቀጣቸው እነርሱን እንዲያጠምቅ እየጠየቁት ነበር ነገር ግን ኃጢአት መስራታቸውን ማቆም አልፈለጉም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእግዚአብሔር ቁጣ በእንዲህ ዓይነት መንገድ መሸሽ አትችሉም!” ወይም “ከእግዚአብሔር ቁጣ በመጠመቅ ብቻ ማምለጥ አትችሉም!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከሚመጣው ቁጣ

“ቁጣ” የሚለው ቃል እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን ቅጣት ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል ምክንያቱም የእርሱ ቁጣ ይቀድመዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እየላከ ካለው ቅጣት” ወይም “እርሱ ሊተገብረው ካለው ከእግዚአብሔር ቁጣ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)