am_tn/luk/03/05.md

1.5 KiB

ሸለቆው ሁሉ ይሞላል… ተራራው እና ኮረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል

ሰዎች በጣም ወደ እነርሱ እየመጣ ላለ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ሰው መንገድ ሲያዘጋጁ፣ ከፍተኛ ቦታዎችን ይቆርጡና መንገዱ ደልዳላ እንዲሆን ዝቅተኛ ቦታዎችን ይሞላሉ፡፡ ይህ በፊተኛው ጥቅስ ውስጥ የተጀመረው ተለዋጭ ዘይቤ አካል ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሸለቆው ሁሉ ይሞላል

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመንገዱ ውስጥ ዝቅተኛ ቦታውን ሁሉ ይሞላሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ተራራው እና ኮረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተራራውን እና ኮረብታውን ሁሉ ደልዳላ ያደርጋሉ” ወይም “በመንገዱ ውስጥ ከፍተኛ ቦታውን ሁሉ ያስወግዳሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን ማዳን ማየት

ይህ እንደ ድርጊት ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እንዴት ሰዎችን ከኃጢአት እንደሚያድን ማወቅ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)