am_tn/luk/03/04.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

ጸሐፊው ሉቃስ መጥምቁ ዮሐንስን የሚመለከት ምንባብ ከነቢዩ ኢሳይያስ ጠቀሰ፡፡

በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ እንደ ተፃፈ

እነዚህ ቃላቶች ከነቢዩ ኢሳይያስ የተወሰደ ጥቅስ ያቀርባሉ፡፡ እነርሱ በገቢር/አድራጊ ቅርፅ ሊገለፁ ይችላሉ፣ የትዘለሉት ቃላቶችም መቅረብ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ ነቢዩ ኢሳይያስ የእርሱን ቃላት በያዘውን መጽሐፍ እንደፃፈው እንደዚያው ሆነ” ወይም “ዮሐንስ ነቢዩ ኢሳይያስ በመፅሀፉ የፃፈውን መልእክት ፈፀመ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

በበረሃ ውስጥ የሚጮኽ የአንድ ሰው ድምፅ

ይህ እንደ አረፍተ ሀሳብ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በበረሃ ውስጥ የሚጮኽ የአንድ ሰው ድምፅ ተሰማ” ወይም “እነርሱ በበረሃ ውስጥ የሚጮኽ የአንድ ሰው ድምፅ ሰሙ”

የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናውንም አቅኑ

ሁለተኛው ትእዚያዝ ለመጀመሪያው በይበልጥ ዝርዝር ይጨምርለታል ወይም ያብራራዋል፡፡

የጌታን መንገድ አዘጋጁ

“ለጌታ መንገዱን አዘጋጁ፡፡” ይህን ማድረግ የጌታ መልእክት ሲመጣ ለመስማት መዘጋጀትን ይወክላል፡፡ ሰዎች ከኀጢአታቸው ንስሀ በመግባት ይህን ያደርጉታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ሲመጣ የጌታን መልእክት ለመስማት ተዘጋጅ” ወይም “ንስሀ ግባ፣ ለሚመጣው ጌታ የተዘጋጀህ ሁን” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገድ

“መተላለፊያ” ወይም “ጎዳና”