am_tn/luk/02/48.md

2.8 KiB

ሲያዩት

“ማርያምና ዮሴፍ ኢየሱስን ሲያገኙት”

ለምን እንዲህ ታደርገናለህ?

ይህ ቀጥተኛ ያልሆነ ተግሳጽ ነው ይህም እነርሱ ወደ ቤት ሲሄዱ አብሯቸው ስላልነበረ ነው፡፡ ይህ ስለ እርሱ እንዲጨነቁ አድርጓቸው ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛን እንዲህ እንድንሆን ማድረግ አልነበረብህም!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ስሙ

ይህ ቃል ብዙ ጊዜ አንድ አዲስ ወይም ወሳኝ የሆነ ሁነት ሊጀምር መሆኑን ለማሳየት ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ አዲስ ድርጊት የት እንደሚጀምር ላማሳየት ሊጠቅም ይችላል፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ በእንዲህ ዓይነት መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ሀረግ ካለው እዚህ ላይ ለመጠቀም አግባብነት ያለው መሆኑን አስብ።

ለምን ፈለጋችሁኝ?

ኢየሱስ ወላጆቹን በለስላሴው ለመገሰጽ ሁለት ጥያቄዎችን ይጠቀማል፣ እነርሱ ያልተረዱት በሰማይ ያለው አባቱ የሰጠው ዓላማ እንዳለም ይነግራቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ እኔ መጨነቅ የለባችሁም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

(… ማድረግ) እንዳለብኝ …. አታውቁም?

ኢየሱስ ወላጆቹ አባቱ ሊያደርገው የሰጠው ዓላማ እንዳለ ማወቅ እንዳለባቸው ለመንገር ሁለተኛውን ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ “(ማድረግ) እንዳለብኝ ማወቅ ነበረባችሁ” አማራጭ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ አባቴ ስራ

የዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉ 1) ኢየሱስ እነዚህን ቃላት በጥንቃቄ መርጦ የተናገረው አባቱ የሰጠውን ስራ እየሰራ እንደሆነ ለማሳየት ነው፣ ወይም 2) እነዚህ ቃላት ኢየሱስ የነበረበትን ቦታ፣ “የአባቴ ቤት” የሚያስረዳ ፈሊጥ ነው፡፡ ቀጣዩ ቁጥር የኢየሱስ ወላጆች ኢየሱስ የሚነግራቸውን ነገሮች አልተረዱትም ስለሚል ይህን ከዚህ በላይ ለማብራራት ባይሞከር ጥሩ ነው፡፡

የአባቴን ስራ

የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ፣ በ12 አመቱ የእውነት አባቱ የማርያም ባል የነበረው ዮሴፍ ሳይሆን እግዚአብሔር እንደነበር አስተውሎ ነበር፡፡ (ልጅ እና አባትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)