am_tn/luk/02/45.md

1.6 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ የተከሰተን ወሳኝ ክስተት ያሳያል፡፡ ቋንቋችሁ እንደዚህ ዓይነትን ነገር ማሳያ መንገድ ካለው እሱን መጠቀም ይቻላል፡፡

በቤተ መቅደስ

ይህ የመቅደሱ ቅጥር ግቢን ያሳያል፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ ውስጥ መግባት የሚችሉት ካህናት ብቻ ነበሩ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ” ወይም “በቤተ መቅደስ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በመካከል

ይህ ቃለ በቃል መሃል ላይ ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም “አብሮ ሆኖ” ፣ “በእነርሱ መካከል” ወይም “በእነርሱ ተከብቦ” የሚለውን ትርጉም ይይዛል፡፡

አስተማሪዎቹ

“የኃይማኖት መምህሮች” ወይም “ስለ እግዚአብሔር ለሰዎች ያስተምሩ የነበሩ”

የሰሙት ሁሉ ይገረሙ ነበር

12 ዓመቱ የሆነና፣ የኃይማኖት ትምህርት ያልተማረ አንድ ልጅ በጥሩ ሁኔታ ጥያቄዎችን መመለስ መቻሉ እንዴት እንደሆነ አልገባቸውም፡፡

በማስተዋሉ

“ምን ያህል ማስተዋል በመቻሉ” ወይም “ስለ እግዚአብሔር ብዙ ማስተዋል በመቻሉ”

መልሶቹ

“እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደመለሰላቸው” ወይም “ጥያቄዎቻቸውን በጥሩ ሁኔታ በመመለሱ”