am_tn/luk/02/30.md

2.2 KiB

ዓይኖቼ አይተዋል

ይህ አገላለጽ “በግሌ አይቻለሁ” ወይም “እኔ እራሴ አይቻለሁ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ማዳንህን

ይህ አገላለጽ ድነትን የሚያመጣውን ሰው ስምኦን በእጁ ይዞት የነበረውን ሕጻኑን ኢየሱን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የላክከውን አዳኝ” ወይም “እንዲያድን የላክከውን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ የላክኸው

የቀደመው ሐረግ እንደተተረጎመት አተረጓጎም፣ ይህ “አንተ የላክኸውን” ወደሚለው ሊለወጥ ይችላል።

ያዘጋጀኸውን

“ያሰብከውን” ወይም “እንዲከሰት ያደረግከውን”

ለአህዛብ የሚገልጥ ብርሃን

ይህ ዘይቤ ሕጻኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅና መረዳት እንዲችሉ ይረዳቸዋል የሚለውን ይገልጻል፡፡ እዚህ ላይ የአሕዛብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳት ሰዎች አንድን ቁስ ለማየት ብርሃንን እንደሚጠቀሙት ተደርጎ ተመስሎ ቀርቧል፡፡ አሕዛብ የሚመለከቱት ምን እንደሆነ በግልጽ ማሳየት አለብህ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ ሕጻን ብርሃን ሰዎች አጥርተው መመልከት እንዲችሉ እንደሚያደርግ፣ ልክ እንደዛ እርሱም አሕዛብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲሁ እንዲያውቁ ይረዳቸዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚገልጥ

የሚገለጠው ነገር ምን እንደሆነ በግልጽ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእግዚአብሔርን እውነት የሚገልጥ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሕዝብህ ለእስራኤል ክብር

“እርሱ ለሕዝብህ ለእስራኤል ክብር መምጣት ምክንያት ይሆናል”