am_tn/luk/02/25.md

2.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ማርያምና ዮሴፍ በቤተ መቅደስ ውስጥ እያሉ ሁለት ሰዎች ያገኛሉ፣ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያመሰግነውና ስለሕጻኑ ትንቢትን የተናገረው ስምኦንና ነብይቷ ሃና ናቸው፡፡

እነሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል በታሪኩ ውስጥ አዲስ ውስጥ አዲስ ሰውን ያስተዋውቃል፡፡ ቋንቋችሁ ይህንን ማሳያ የራሱ መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡ (የአዲስና የቀድሞ ተሳታፊዎች መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

ጻድቅና ትጉ ነበር

እነዚህ ረቂቅ ቃላት እንደ ድርጊት ተደርገው መገለጽ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጽድቅን ይፈጽም ነበር፣ እግዚአብሔርንም ይፈራ ነበር” ወይም “የእግዚአብሔርን ሕግ ይታዘዝ ነበር እግዚአብሔርንም ይፈራ ነበር፡፡

የእስራኤል መጽናናት

“እስራኤል” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ “ማጽናናት” ማለት አንድን ሰው “ማበረታታት” ነው፡፡ “የእስራኤል መጽናናት” ማለት ክርስቶስ ወይም መሲሑ ለእስራኤል ሕዝብ የሚያመጣውን መጽናናት የሚወክል ሐረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤል ሕዝብን የሚያጽናናው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ነበር

“መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር ነበር” እግዚአብሔር በተለየ መንገድ ከእርሱ ጋር ነበር፣ በሕይወትም ጥበብና ምሪትን ይሰጠው ነበር፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር

ይህ በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መንፈስ ቅዱስ አሳይቶት ነበር” ወይም “መንፈስ ቅዱስ ነግሮት ነበር” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በጌታ የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንደማያይ

“ሳይሞት በፊት በጌታ የተቀባውን መሲህ ያየዋል”