am_tn/luk/02/06.md

2.6 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ይህ የኢየሱስን ውልደትን እና ለበግ ጠባቂዎች የመላዕክቱን ብስራት ይናገራል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፦

ዩዲቢ የሚባለው ትርጉም (እነ ዮሴፍ) የቆዩበትን ቦታ ዝርዝር መረጃ ለመጠበቅ ሲባል እነዚህን ቁጥሮች ቅደም ተከተላቸውን በመቀያየር አንድ መሸጋገርያ ቁጥር አድርጓቸዋል፡፡ (የጥቅስ ድልድዮች የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ ቀጣዩ ክስተት መጀመሩን ያሳያል፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያም ሳሉ

“ማርያምና ዮሴፍ በቤተልሔም እያሉ”

ልጇን የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ

“ልጇን የምትገላገልበት ጊዜ ደረሰ”

በረዥም የጨርቅ ብጣሽ ጠቀለለችው

በአንዳንድ ባህሎች እናቶች ልጆቻቸውን በጨርቅ ወይም በብርድ ልብስ በመጠቅለል እንዲመቻቸው ያደርጋሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሙሉ ሰውነቱን በጨርቅ ጠቀለለችው” ወይም “በብርድ ልብስ አጥብቃ ጠቀለለችው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በግርግም አስቀመጠችው

ይህ በተለየ ሁኔታ የሚሰራ እንስሶች እንዲበሉ መኖ ወይም ሌላ የከብት ምግብ የሚቀመጥበት የምግብ ማስቀመጫ ሳጥን ነገር ነው፡፡ ንጹህ እንደነበረና ለስላሳና ጠንከር ያለ ለሕጻኑ የሚመች መተኛ የሚሆን የሳር ድርቆሽ ክምር እንደነበረው ይገመታል፡፡ ከብቶች ከዋናው ቤት ሳይርቅ ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ መኖርያ ይሰራላቸዋል፣ ይህም እነርሱን ለመመገብና ለመጠበቅ እንዲመች ነው፡፡ ማርያምና ዮሴፍ በእንስሳት መኖርያ ውስጥ ነበር ይቆዩ የነበረው፡፡

በእንግዶች ማረፍያ ውስጥ ለእነርሱ ቦታ አልነበረም

“በእንግዶ ማረፍያ ክፍል ውስጥ እነርሱ ሊያርፉ የሚችሉበት ቦታ አልነበረም” ቦታ ያለመኖሩ ምክንያት ብዙ ሰዎች ለመመዝገብ ወደ ቤተልሔም መጓዛቸው እንደሆነ ይገመታል፡፡ ሉቃስ ይህንን እንደ ተጨማሪ የጀርባ መረጃ ይናገራል፡፡ (የጀርባ ታሪክ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)