am_tn/luk/02/04.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

ዩዲቢ የሚባለው ትርጉም አርፍተ ነገሮቹን ለማሳጠር እነዚህን ሁለት ቁጥሮች አንድ ላይ በማድረግ አንድ የመሸጋገርያ ቁጥር አድርገዋቸዋል፡፡ (የጥቅስ ድልድዮች የሚለውን ይመልከቱ)

ዮሴፍም

ይህ ዮሴፍን በታሪኩ ውስጥ እንደ አንድ ተሳታፊ አድርጎ ያስተዋውቀዋል፡፡ (የአዲስና የቀድሞ ተሳታፊዎች መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤተልሔም ወደተባለችው የዳዊት ከተማ

“የዳዊት ከተማ” የሚለው ሐረግ ቤተልሔም ምን አይነት ወሳኝ ከተማ እንደሆነች የሚያሳይ የቤተልሔም ከተማ ስም ነው፡፡ ምንም እንኳ ትንሽ ከተማ ብትሆንም ንጉሥ ዳዊት የተወለደው በዚች ከተማ ነው፣ መሲሑም በዚው ከተማ እንደሚወለድ የሚናገር ትንቢት ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የንጉሥ ዳዊት ከተማ ወደነበረችው ወደ ቤተልሔም” ወይም “ንጉሥ ዳዊት ወደተወለደበት ከተማ ወደ ቤተልሔም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የዳዊት ወገንና ቤት ስለነበር

“ምክንያቱም ዮሴፍ የዳዊት ዘር ስለነበር”

ለመጻፍ

ይህ ማለት በሕዝብ ቆጠራው ውስጥ እንዲያካትቱት ለመንግስቱ ሹማምንት ለማሳወቅ ማለት ነው፡፡ የሚቻል ከሆነ የመንግስት የሕዝብ ቆጠራን የሚገልጽ ቃል ተጠቀም፡፡

ከማርያም ጋር

ማርያም ከዮሴፍ ጋር ከናዝሬት ተነስታ ተጉዛ ነበር፡፡ ሴቶችም እንደወንዶች ቀረጥ ይጣልባቸው ስለነበረ እርሷም አብራ ተጉዛ መመዝገብ ነበረባት፡፡ (የአዲስና የቀድሞ ተሳታፊዎች መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ ታጭታ የነበረችው

“እጮኛው” ወይም “ለእርሱ ቃል ገብታለት የነበረች” እጮኛ የነበሩ ጥንዶች በሕግ እንደተጋቡ ተደርገው ይታሰባሉ ነገር ግን በመካከላቸው ምንም አይነት አካላዊ ግንኙነት አይኖርም ነበር፡፡