am_tn/luk/01/80.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

ይህ ዮሐንስ እያደገ ስለመጣባቸው አመታት ይናገራል፡፡

አሁን

ይህ ቃል ዋናው የታሪክ መስመር መቋረጡን ያመለክታል፡፡ ሉቃስ ስለ ዮሐንስ ውልደት ከመናገር በፍጥነት ወጥቶ ዮሐንስ አድጎ ያደርግ ስለነበረው አገልግሎት ይናገራል፡፡

በመንፈስ ጠነከረ

“በመንፈስ እየበሰለ መጣ” ወይም “ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት አጠነከረ”

በምድረ በዳ ነበር

“በምድረ በዳ ኖረ” ሉቃስ ዮሐንስ በምን እድሜ ላይ በምድረ በዳ መኖር እንደጀመረ አይናገርም፡፡

እስከ ታየበት ቀን ድረስ

ይህ ከጊዜ ጋር በተያያዘ ያቆመበትን ነጥብ የግድ አያመለክትም፡፡ ዮሐንስ በአደባባይ መስበክ ከጀመረ በኋላም እንኳ ቢሆን በምድረ በዳ ይኖር ነበር፡፡

በአደባባይ መታይ እስኪጀምር

“በአደባባይ መስበክ እስከሚጀምር ድረስ”

እስከጀመረበት ቀን

ይህ በጠቅላላው “ጊዜውን” እና “ሁኔታውን” ለመናገር ጥቅም ላይ ነው የዋለው፡፡