am_tn/luk/01/78.md

2.5 KiB

በአምላካችን ርህራሄና ምህረት

የእግዚአብሔር ምህረት ሰዎችን እንደሚረዳ መግለጽ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእኛ ሩህሩህና መሃሪ ስለሆነ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከላይ የመጣ የጸሐይ ብርሃን …. እንዲያበራ

ብርሃን ብዙ ጊዜ የእውነት ምሳሌ ነው፡፡ እዚህ ላይ አዳኙ ለእኛ የሚሰጠው መንፈሳዊ እውነት ዓለምን ሁሉ በብርሃን የሚሞላ የጸሐይ ብርሃን ተደርጎ ተመስሏለ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማብራት

“እውቀት መስጠት” ወይም “መንፈሳዊ ብርሃንን መስጠት”

በጨለማ ለተቀመጡ

ጨለማ እዚህ ላይ የመንፈሳዊ እውነት እጦትን ወይም አለመገኘትን ይወክላል፡፡ እዚህ ላይ መንፈሳዊ እውነት የሌላቸው ሰዎች በጨለማ ውስጥ እንደተቀመጡ ተደርገው ተመስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እውነትን የማያውቁ ሕዝቦች” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጨለማ … የሞት ጥላ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ላይ በመሆን እግዚአብሔር ምህረቱን ለእነርሱ ከማድረጉ በፊት ሰዎች ላይ የነበረውን ጥልቅ ጨለማ አስከፊነት ይገልጻሉ፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በሞት ጥላ

ጥላ ብዙ ጊዜ ሊመጣ ያለውን ነገር ይገልጻል፡፡ እዚህ ላይ እየመጣ ያለን ሞትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሊሞቱ ያሉ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮቻችንም በሰላም መንገድ ይመራል

እዚህ ላይ “መምራት” የሚለው ቃል ማስተማር ለሚለው ቃል ዘይቤ ነው፣ “የሰላም መንገድ” የሚለው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በሰላም መኖርን የሚወክል ዘይቤ ነው፡፡ “እግሮቻችንን” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ሙሉ ማንነት የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእግዚአብሔር ጋር በሰላም መኖርን ያስተምረናል”(ተለዋጭ ዘይቤ እና ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)