am_tn/luk/01/69.md

2.5 KiB

የመዳንን ቀንድ አስነስቶልናል

የአንድ እንስሳ ቀንድ ራስን የመከላከል አቅሙን የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ ማስነሳት ማለት ደግሞ ያልነበረን ማኖር ወይም አንድን ድርጊት መጀመርን ያሳይል፡፡ እዚህ ላይ መሲሑ እስራኤልን የማዳን ኃይል እንዳለው እንደ ቀንድ ምሳሌ ተደርጎ ተመስሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “(እግዚአብሔር) እኛን የማዳን ኃይል ያለውን ሰው ሰጥቶናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በአገልጋዩ በዳዊት ቤት

“የዳዊት ቤት” የሚወክለው ቤተሰቡን ነው በተለይም ደግሞ ዘሮቹን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአገልጋዩ በዳዊት ቤተሰብ” ወይም “የአገልጋዩ ዳዊት ዘር የሆነ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እንደተናገረ

“እግዚአብሔር እንዳለው”

ድሮ በነበሩት በነብያቱ አፍ እንደተናገረው

እግዚአብሔር በነብያቱ አፍ ተናገረ የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔር ነብያቱን እርሱ እንዲላቸው የፈለገውን እንዲናገሩ ማድረጉን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሮ የኖሩትን ቅዱሳን ነብያቱን እንዲናገሩ ያደረጋቸውን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ድሮ የኖሩትን … ማዳኑ ከጠላቶቻችን ነው

“ማዳን” የሚለው ረቂቅ ቃል “መታደግ” እና “ማትረፍ” በሚሉት ግሶች ተለውጦ መገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሮ የኖሩትን …. እርሱም ከጠላቶቻችን ይታደገናል፡፡” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከሚጠሉን … ከጠላቶቻችን

እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ይይዛሉ፣ የተደጋገሙትም ጠላቶቻቸው ምን ያህል ይቃወሟቸው እንደነበረ አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

እጅ

እጅ የሚለው ቃል አንድ ሰው ኃይሉን የሚለማመድበትን እጅ የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃይል” ወይም “ቁጥጥር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)