am_tn/luk/01/64.md

3.9 KiB

አፉ ተከፈተ … ምላሱም ተፈታ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ዘካርያስ በድንገት መናገር መቻሉን አጽንኦት ይሰጣሉ፡፡ (ፈሊጥ እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አፉ ተከፈተ እና ምላሱም ተፈታ

እነዚህ ሐረጎች በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አፉን ከፈተለት ምላሱንም ፈታለት” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ አካባቢ ይኖሩ በነበሩ ላይ ሁሉ ፍርሃት ሆነ

“ከዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ አካባቢ ይኖሩ በነበሩ ላይ ሁሉ” ለምን ፈርተው እንደነበር ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእነርሱ አካባቢ ይኖሩ የነበሩት ሁሉ እግዚአብሔር ለዘካርያስ እንዲህ በማድረጉ በእግዚአብሔር እጅግ ተደነቁ“ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ አካባቢ ይኖሩ በነበሩ ላይ

“ሁሉ” የሚለው ቃል ጅምላ ፍረጃ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ” ወይም “በዚያ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ብዙ ሰዎች” (ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ነገሮች መከሰታቸው በይሁዳ ተራራማው ከተማ ሁሉ ተዳረሰ

“እነዚህ ነገሮች መከሰታቸው … ተዳረሰ” የሚለው ሐረግ ሰዎች ስለ እነርሱ ማውራታቸውን የሚያሳይ ዘይቤ ነው፡፡ ጥቅም ላይ የዋለው ተደራጊ ቅርጽ በአድራጊ ቅርጽ መቀየር ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ተራራማው ከተማ ይኖሩ በነበሩ ሰዎች ይወሩ ነበር” ወይም “በይሁዳ ተራራማው ከተማ የሚገኙ ሕዝቦች ስለ እነዚህ ነገሮች ያወሩ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰሟቸው ሁሉ

“ስለተከሰቱት ነገሮች የሰሙ በሙሉ”

በልባቸው አኖሯቸው

ስለ ተከሰቱ ነገሮች ነገር ደጋግሞ ማሰላሰልና ማሰብ ነገሮቹን በልብ ውስጥ በጥንቃቄ እንደማኖር ተደርጎ ይታሰባል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ እነዚህ ነገሮች በጥንቃቄ ያስቡና ያሰላስሉ ነበር” ወይም “ስለ እነዚህ ክስተቶች ደጋግመው ያስቡ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እያሉ በልባቸው አኖሯቸው

“እየጠየቁ በልባቸው አኖሯቸው”

ይሄ ሕጻን ምን ይሆን ይሆን?

“ይህ ሕጻን አድጎ ምን ዓይነት ልዩ ሰው ይሆን ይሆን?” ይህ ጥያቄ ሰዎቹ ስለ ሕጻኑ በሰሙት ነገሮች ያደረባቸውን መገረም ለመግለጽ የተጠቀሙበት መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይሄ ልጅ አድጎ ምን ዓይነት ልዩ ሰው ይሆን ይሆን?” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበር

“የአምላክ እጅ” የሚለው ሐረግ የአምላክን ኃይል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአምላክ ኃይል ከእርሱ ጋር ነበር” ወይም “አምላክ በእርሱ ውስጥ በኃይል ይሰራ ነበር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)