am_tn/luk/01/59.md

1.5 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ እዚህ ላይ ዋናው የታሪክ መስመር ተቆርጦ ሌላ ታሪክ ሊነገር መጀመሩን ለማሳየት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ እዚህ ላይ ሉቃስ አዲስ ታሪክ መናገር ይጀምራል፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

በስምንተኛው ቀን

እዚህ ላይ “ስምንተኛው ቀን” የሚለው ቃል ከሕጻኑ ውልደት በኋላ ያለውን ቀን ያሳያል ይህም ከመጀመርያው ቀን ጀምሮ ወይም ሕጻኑ ከተወለደበት ጀምሮ ተቆጥሮ ያለውን ቀን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሕጻኑ ሕይወት በስምንተኛው ቀን” (ደረጃ የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

ሕጻኑን ሊገርዙት መጡ

ይህ ብዙ ጊዜ አንድ ሰው ልጁን በሚገርዝበት ጊዜ ወዳጆቹ በዚያ ተገኝተው ከቤተሰቡ ጋር ሆነው የሚያከብሩበት ስነ ስርዓት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሕጻኑ የግርዘት ሥርዓት መጡ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

… ብለው ሊጠሩት ነበር

“… ብለው ስም ሊያወጡለት ነበር” ወይም “… የሚል ስም ሊሰጡት ፈልገው ነበር”

በአባቱ ስም

“የአባቱን ስም”

በዚህ ስም

“በዚያ ስም” ወይም “በተመሳሳይ ስም”