am_tn/luk/01/52.md

1.6 KiB

ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዷል

ዙፋን ማለት ገዢ የሚቀመጥበት ወንበር ነው፣ ወንበሩ የስልጣኑም ምልክት ነው፡፡ ገዢ ከዙፋኑ ከወረደ በኋላ ሊገዛበት የሚችል ስልጣን የለውም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የገዢዎችን ስልጣን ወስዷል” ወይም “ገዢዎች መግዛትን እንዲያቆሙ አድርጓቸዋል” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝቅ ያሉትንም ከፍ አደረጋቸው

በዚህ የቃላት መግለጫ መሰረት፣ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ሰዎች ዝቅተኛ ስፍራ ካላቸው ይልቅ እጅግ ከፍ ያሉ እንደሆኑ ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፡- “ትሁት ሰዎችን ታላቅ አደረጋቸው” ወይም “ሌሎች ሰዎች ያላከበሯቸውን ሰዎች እርሱ አከበራቸው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝቅ ያሉትን

“በድህነት ውስጥ ያሉትን።” ይህ በሉቃስ 1:48 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡

የተራቡትን መግቧል … ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ልኳቸዋል

በእነዚህ ተቃራኒ ድርጊቶች መካከል ያለው ልዩነት ከተቻለ በትርጉሙ ላይ ግልጽ ይደረግ፡፡

የተራቡትን በመልካም ነገር አጠገበ

የዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1) “ለተራቡት ጥሩ የሚበላ ምግብ ሰጣቸው” ወይም 2) “ለተቸገሩት መልካምን ነገር ሰጣቸው”