am_tn/luk/01/46.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

ማርያም ለአምላኳና ለአዳኟ የምስጋናን መዝሙር መዘመር ትጀምራለች፡፡

ነፍሴ ታመሰግነዋለች … መንፈሴም ሐሴት ታደርጋለች

ሁለቱም “ነፍስ” እና “መንፈስ” የአንድ ሰው መንፈሳዊ ማንነት አካላት ናቸው፡፡ ማርያም አምልኮዋ ከውስጥ የመነጨ እንደሆነ ለማሳየት እንደዚህ ብላለች፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የውስጥ ማንነቴ ያምሰግናል … ልቤም እጅግ ሐሴትን አድርጓል” ወይም “አመሰግናለሁ … ሐሴትም አደርጋለሁ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

በ … ሐሴትን አድርጋለች

“በ … እጅግ ደስታ ተሰምቷታል” ወይም “በ … እጅግ ተደስታለች”

አዳኜ እግዚአብሔር

“እኔን ያዳነኝ እግዚአብሔር” ወይም “የሚያደነኝ እግዚአብሔር”