am_tn/luk/01/42.md

4.4 KiB

ድምጿን ከፍ አድርጋ … በጩኸት ተናገረች

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲይዙ ኤልሳቤጥ ምን ያህል ደስተኛ እንደነበረች አጽንኦት ይሰጣሉ፡፡ሁለቱን አደባልቆ አንድ ሐረግ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአድናቆት ጮኸች” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ድምጿን ከፍ አደረገች

ይህ ፈሊጥ “ድምፁዋን አጩሃ ተናገረች” የሚለውን ትርጉም የያዘ ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ

“ከሴቶች መካከል” የሚለው ፈሊጥ “ከሌላ ሴት በሙሉ የተሻለች” የሚለውን ትርጉም ይይዛል፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የማሕጸንሽ ፍሬ

የማርያም ልጅ እዚህ ላይ አንድ ተክል እንደሚያፈራው ፍሬ ተደርጎ ተጽፏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በማሕጸንሽ ውስጥ ያለው ሕጻን” ወይም “የምታረግዥው ሕጻን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ሆነልኝ?

ኤልሳቤጥ መልስ ፈልጋ ጥያቄን እየጠየቀች አይደለም፡፡ የጌታ እናት ወደ እርሷ በመምጣቷ ምን ያህል እንደተደነቀችና ደስተኛ እንደነበረች እያሳየች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጌታዬ እናት ወደ እኔ መምጣቷ እንዴት የሚደንቅ ነው!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የጌታዬ እናት

ኤልሳቤጥ ማርያምን “የጌታዬ እናት” ብላ እንደጠራቻት “አንቺ” የሚለውን መግለጫ በመጨመር የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንቺ የጌታዬ እናት” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

ይህ ኤልሳቤጥ ቀጥላ ለምትናገረው አስገራሚ ነገር ማርያም ትኩረት እንድትሰጥ የሚናገር ቃል ነው፡፡

የሰላምታሽ ድምጽ ወደ ጆሮዬ በደረሰ ጊዜ

የአንድን ነገር ድምጽ መስማትን “ድምጹ ወደ ጆሮ ደረሰ” በማለት ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰላምታሽን ድምጽ በሰማሁ ጊዜ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በደስታ ዘለለ

“በድንገት በደስታ ተንቀሳቀሰ” ወይም “በጣም ከመደሰቱ የተነሳ በኃይል ዞረ”

ከጌታ የተነገራትን የምታምን የተባረከች ናት

ኤልሳቤጥ ለማርያም ስለ ራሷ ስለ ማርያም ነበር የምትነግራት። አማራጭ ትርጉም፡-“ከጌታ የተነገረሽን የምታምኚ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ወይም ሶስተኛ መደብ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የምታምን ᎐᎐᎐ የተባረከች ናት

በተደራጊ ቅርጽ የተቀመጠው ግስ በአድራጊ ቅርጽ መቀመጥ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ስላመነች እግዚአብሔር ይባርካታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የእነዚህ ነገሮች ፍጻሜ ይሆናልና

“እነዚህ ነገሮቸ በእርግጠኝነት ይፈጸማሉ” ወይም “እነዚህ ነገሮች እውን ይሆናሉ”

ከጌታ ለእርሷ የተነገሯት ነገሮች

መልእክቱን ሲናገር የሰማችው መልአኩ ገብርኤልን ነው (ሉቃስ 1፡26 ይመልከቱ)፣ ነገር ግን መልእክቱ (“እነዚህ ነገሮች”) በዋነኛነት የመጣው ከጌታ ነበር። ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ከጌታ የሰማችው መልእክት” ወይም “መልአኩ የነገራት የጌታ መልእክት” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)