am_tn/luk/01/34.md

2.0 KiB

ይህ እንዴት ይሆናል

ምንም እንኳ ማርያም ነገሩ እንዴት እንደሚከሰት ባይገባትም፣ መከሰቱን ግን አልተጠራጠረችም፡፡

ከማንም ጋር ተኝቼ አላውቅም

ማርያም ይህንን ትህትና የተሞላበት አገላለጽ የተጠቀመችው እርሷ ከማንም ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ፈጽማ እንደማታውቅ ለመግለጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድንግል ነኝ” (ለስላሴ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይሆናል

የማርያም እርግዝና የሚጀምረው መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሷ በመምጣት ነው፡፡

በአንቺ ላይ ይሆናል

“ይቆጣጠርሻል”

የልዑልም ኃይል

ማርያም ድንግል እያለች ከተፈጥሮ በላይ በሆነ ሁኔታ እንድታረግዝ የሚያደርጋት የእግዚአብሔር “ኃይል” ነበር፡፡ይህ አካላዊ ወይም ወሲባዊ ትርጉም ያለው እንዳይመስል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፣ ይህ ተዓምር ነበር፡፡

በአንቺ ላይ ይሆናል

“እንደ ጥላ ይከልልሻል”

የሚወለደውም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል

ይህ በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚወለደውንም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ብለው ይጠሩታል” ወይም “የሚወለደውም ሕጻን ቅዱስ ይሆናል፣ ሰዎችም የእግዚአብሔር ልጅ ብለው ይጠሩታል፡፡ (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅዱሱ

“ቅዱሱ ልጅ” ወይም “ቅዱሱ ሕጻን”

የእግዚአብሔር ልጅ

ይህ ለኢየሱስ የተሰጠ ልዩ መጠርያ ማዕረግ ነው፡፡ (ልጅ እና አባትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)