am_tn/luk/01/30.md

2.5 KiB

ማርያም ሆይ አትፍሪ

መልዓኩ ማርያም እርሱን አይታ እንድትፈራ አይፈልግም ምክንያቱም እግዚአብሔር መልካም መልዕክትን እንዲያደርስ ስለላከው ነው፡፡

በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻል

“ሞገስን ማግኘት” የሚለው ፈሊጥ በአንድ ሰው ዘንድ መልካም ተቀባይነትን ማግኘት ነው፡፡ የአርፍተ ነገሩን ቅደም ተከተል በመቀየር እግዚአብሔርን የድርጊቱ ባለቤት አድርጎ ማሳየት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ጸጋውን ሊሰጥሽ ወስኗል” ወይም “እግዚአብሔር ቸርነቱን ላንቺ እያሳየ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ … ኢየሱስ … የልዑል ልጅ

ማርያም “ወንድ ልጅን” ትወልዳልች ስሙም “የልዑል ልጅ” ይባላል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ከሰው እናት የተወለደ የሰው ልጅ ነው፣ እርሱ የእግዚአብሔርም ልጅ ነው፡፡ እነዚህ ቃላት በጥንቃቄ መተርጎም አለባቸው፡፡

ይባላል

የዚህ ትርጉሞች ሊሆኑ የሚችሉት 1) “ሰዎች … ብለው ይጠሩታል” 2) “እግዚአብሔር … ይጠራዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የልዑል ልጅ

ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ለሆነው ለኢየሱስ እጅግ ወሳኝ የሆነ ስያሜ ነው፡፡ (ልጅ እና አባትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል

ዙፋን የሚየያሳየው የንጉስን የመግዛት ስልጣን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አባቱ ዳዊት ይገዛ እንደነበር እርሱም እንዲገዛ ስልጣንን ይሰጠዋል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ለመንግሥቱም መጨረሻ አይኖርም

“መጨረሻ አይኖርም” የሚለው አሉታዊ መግለጫ ለዘላለም የሚቀጥል መሆኑን አጽንኦት ይሰጣል፡፡ አርፍተ ነገሩ በአዎንታዊ ሐረግ መገለጽ ይችላል፡፡ “መንግስቱ እስከመጨረሻ አያበቃም” አማራጭ ትርጉም፡- (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)