am_tn/luk/01/24.md

1.5 KiB

ከነዚህም ቀናት በኋላ

“እነዚህ ቀናት” የሚለው ሐረግ ዘካርያስ በቤተመቅደስ ውስጥ ያገለገለባቸውን ቀናት ያመለክታል፡፡ ይህ ምንን እንደሚያመለክት የበለጠ ግልጽ አድርጎ ማስረዳት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዘካርያስ በቤተመቅደስ ካገለገለበት ጊዜ በኋላ” (የአዲስ ሁነት መግቢያ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሚስቱ

“የዘካርያስ ሚስት”

ራሷን ደበቀች

“ከቤት አልወጣችም” ወይም “ ብቻዋን ቆየች”

ጌታ እንዲህ አድርጎልኛል

ይህ ጌታ ልጅ ማርገዝ እንድትችል እንዳስቻላት ያሳያል፡፡

እንዲህ አድርጎልኛል

ይህ አዎንታዊ የሆነ ግነት ነው፡፡ ጌታ ባደረገላት ነገር በጣም ደስተኛ ናት፡፡

በቸርነቱ ተመልክቶኛል

እዚህ ላይ “መመልከት” የሚለው ፈሊጥ ፈሊጥ ሲሆን ትርጉሙም “መንከባከብ” ወይም “በሚገባ መያዝ“ ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፡- “በርህራሄ ተመለከተኝ” ወይም “አዘነልኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቀፌታዬን

ይህ እርሷ ልጆች ባለመውለዷ ይሰማት የነበረውን ነቀፋ ያሳያል፡፡