am_tn/luk/01/21.md

1.4 KiB

አሁን

ይህ በታሪኩ ውስጥ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከተከሰተው ነገር ከቤተ መቅደስ ውጪ ወደተከሰተው ነገር ትኩረቱ መቀየሩን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ እየተከሰተ በነበረ ጊዜ” ወይም “መልዓኩና ዘካርያስ እየተነጋገሩ በነበረ ጊዜ”

በቤተ መቅደስ ውስጥ ራዕይ እንዳየ ተገነዘቡ፡፡ እርሱም ምልክቶችን ያሳያቸው ነበር፣ ዲዳም ሆኖ ቆየ

እነዚህ ነገሮች በተመሳሳይ ሰዓት የተከሰቱ እንደሆን ይገመታል፣ የዘካርያስ ምልክቶችም ሕዝቡ እርሱ ራዕይን እንዳይ እንዲገነዘቡ አድርገዋቸዋል፡፡ የነዚህን ቅደም ተከተል መቀየር አድማጩ የበለጠ መረዳት እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዘካርያስ ምልክቶችን ያሳያቸው ነበር ዲዳም ሆኖ ኖረ፡፡ ስለዚህ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሳለ ራዕይን እንደተመለከተ ሕዝቡ ተገነዘበ”

ራዕይ

ቀድሞ የተሰጠው መግለጫ ገብርኤል በእርግጥም ወደ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደሱ እንደመጣ ያሳያል፡፡ ሕዝቡ ይህንን ባለማወቅ ዘካርያስ ራዕይ እንደተመለከተ አሰቡ፡፡