am_tn/luk/01/16.md

2.9 KiB

ብዙዎቹ የእስራኤል ሕዝቦች ወደ አምላካቸው እግዚአብሔር ይመለሳሉ

እዚህ ላይ “ይመለሳሉ” የሚለው ቃል አንድ ሰው ንስሃ ገብቶ እግዚአብሔርን ማምለክ መጀመርን የሚያመለክት ዘይቤ ነው፡፡ ይህም በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱም ብዙዎች የእስራኤል ሕዝቦችን ንስሐ እንዲገቡና አምላካቸው እግዚአብሔርን እንዲያመለኩ ያደርጋል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በአምላክ ፊት ይሄዳል

ጌታ ከመምጣቱ በፊት፣ ጌታ እንደሚመጣ ለሰዎች ይሰብካል፡፡

በጌታ ፊት

እዚህ ላይ “ፊት” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ሕልውና የሚያሳይ ፈሊጥ ነው፡፡ በአንዳንድ ትርጉሞች ላይ ተጽፎ ላይገኝ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በኤልያስ መንፈስና ኃይል

“ኤልያስ በነበረው መንፈስና ኃይል፡፡” “መንፈስ“ የሚለው የእግዚአብሔርን መንፈስ ወይም ኤልያስ የነበረውን አስተሳሰብ ሊያሳይ ይችላል፡፡ “መንፈስ” የሚለው ቃል የሞትን ወይም የክፉን መንፈስ በሚለው እንዳይተረጎም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች ይመልስ ዘንድ

“አባቶች ስለ ልጆቻቸው እንዲያስቡ ደግሞ ጠየቃቸው” ወይም “አባቶች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያድሱ ዘንድ”

ልባቸውን ይመልሳል

እዚህ ላይ ልብ አቅጣጫውን እንደሚቀይር ነገር ተደርጎ ተቀምጧል፡፡ ይህ የአንድ ሰው አስተሳሰብን ስለመቀየር ያመለክታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ

“የማይታዘዙትን ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ” ወይም “የማይታዘዙት ጠቢብ እንዲሆኑና የጻድቅ ሰዎችን ተግባር እንዲፈጽሙ ለማሳመን”

የማይታዘዙት

ይህ የሚያሳየው ጌታን የማይታዘዙትን ሰዎች ነው፡፡

ለጌታ የተዘጋጁትን ሕዝብ እንዲያሰናዳ

ሕዝቡ ምን ለማድረግ እንደሚዘጋጁ በግልጽ ማሳየት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልዕክቱን ለማመን የተዘጋጁ ሕዝቦችን ለጌታ ማሰናዳት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)