am_tn/luk/01/14.md

1.7 KiB

ታላቅ ይሆናል

“የዚህም ምክንያት ታላቅ ስለሚሆን ነው” ዘካርያስና “ብዙዎች” ደስ የሚላቸው ዮሐንስ “በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ” ስለሚሆን ነው፡፡ ተከትሎ ያለው የቁጥር 15 ክፍል እግዚአብሔር ዮሐንስ እንዴት እንዲኖር እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡

ደስታና ተድላ ይሆንልሃል

“ደስታ” እና “ተድላ” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ይህም ምን ያህል ደስታ እንደሚሆን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ታላቅ ደስታ ይሆንልሃል” ወይም “እጅግ ደስተኛ ትሆናለህ” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በመወለዱም

“በመወለዱ ምክንያትም”

በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናል

“ለጌታ እጅግ ጠቃሚ ሰው ይሆናል” ወይም “እግዚአብሔር እርሱን እጅግ ጠቃሚ ሰው አድርጎ ያየዋል”

በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል

ይህ በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መንፈስ ቅዱስ ኃይልን ይሰጠዋል” ወይም “መንፈስ ቅዱስ ምሪትን ይሰጠዋል፡፡” ይህ አርፍተ ነገር ክፉ መንፈስ ሰውን እንደሚያረገው አይነት እንዳይመስል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በእናቱ ማሕጸን

“ገና በእናቱ ማሕጸን ውስጥ ሳለ” ወይም “ገና ሳይወለድ”