am_tn/luk/01/08.md

2.3 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ ከተሰጠው የጀርባ ታሪክ መረጃ ወደ ሌላ ታሪክ ትኩረት እንደተቀየረ የሚያሳይ ሐረግ ነው፡፡

ዘካርያስ በእግዚአብሔር ፊት የክህነት ስራውን እየሰራ ነበር

ይህ ዘካርያስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መሆኑን፣ የክህነት ስራዎቹም እግዚአብሔርን የማምለክ ስርዓት አካላት መሆናቸውን ያሳያል፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በክፍሉ ተራ

“የእርሱ ቡድን ተራ ሲሆን” ወይም “የእርሱ ቡድን የማገልገል ጊዜያቸው በደረሰ ጊዜ”

እንደ ካህናት ሥርዓት … ዕጣን ለማጠን እጣ ደረሰበት

ይህ ዓረፍተ ነገር ስለ ካህናት ስራዎች መረጃን ይሰጣል፡፡ (የጀርባ ታሪክ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስርዓት

“ባሕላዊው መንገድ” ወይም “ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት”

እጣ ደረሰበት

ምልክት ያለበትን ድንጋይ ወደ መሬት በመጣል እንደ እጣ በማውጣት አንድን ነገር ለመወሰን እንዲረዳቸው ይጠቀሙ ነበር፡፡ ካህናቱ በሚያወጡት እጣ ውስጥ የትኛው ካህንን ለተለያዩ ስራዎች መምረጥ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ምሪትን እንደሚሰጣቸው ያምኑ ነበር፡፡

እጣን ለማጠን

ካህናቱ በየጠዋቱና በየማታው ጣፋጭ ሽታ ያለውን እጣን በመቅደሱ ውስጥ በሚገኝ መሰዊያ ላይ በማቃጠል ለእግዚአብሔር እንደ መስዋዕት ያቀርቡ ነበር፡፡

ሕዝቡ ሁሉ

“ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ” ወይም “ብዙ ሰዎች”

በውጪ

ቅጥር ግቢው ቤተ መቅደሱ ዙሪያ የሚገኝ የተከለለ ቦታ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከቤተ መቅደሱ ሕንጻ ውጪ” ወይም “ከቤተ መቅደሱ ውጪ ባለው ቅጥር ግቢ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)