am_tn/luk/01/01.md

3.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

ሉቃስ ለምን ወደ ቴዎፍሎስ እንደሚጽፍ ያብራራል፡፡

በእኛ ዘንድ ስለተፈጸሙት ነገሮች

“በእኛ መካከል ስለተፈጸሙት ነገሮች” ወይም “በእኛ መካከል ተከስተው ሰለነበሩት ነገሮች”

በእኛ ዘንድ

ቴዎፍሎስ ማን እንደነበር በእርግጠኝነት የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ቴዎፍሎስ ክርስቲያን የነበረ ከሆነ ግን “እኛ” የሚለው ገላጭ እርሱንም ያካትት የነበረ ይሆናል፣ ካልሆነ ግን እርሱን የሚያካትት አይሆንም፡፡ (አካታች “እኛ” እና አግላይ እና አካታች “እኛ” የሚለውን ይመልከቱ)

የቃሉ አገልጋዮችና የዓይን እማኞች የነበሩ

“የዓይን እማኝ” ማለት አንድ ነገር ሲከሰት በዓይኑ የተመለከተ ማለት ነው፣ አገልጋይ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን መልዕክት ለሰዎች በመናገር እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሰው ነው፡፡ እንዴት የቃሉ አገልጋዮች እንደተባሉ ግልጽ አድርጎ መናገር ያስፈልጋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተከሰተውን የተመለከቱና መልዕክቱን በመናገር እግዚአብሔርን ያገለገሉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የቃሉ አገልጋዮች

“ቃሉ” የሚለው ቃል የሚወክለው ከብዙ ቃላት የተገነባ አንድን መልዕክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የመልዕክቱ አገልጋዮች” ወይም “የእግዚአብሔር መልዕክት አገልጋዮች” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

በትክክል አጥንቼ

“ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የተመረመረ።” ሉቃስ በትክክል ምን እንደተከሰተ ለማወቅ በጥንቃቄ ምርምር አድርጓል፡፡ እርሱ ሰለተከሰቱት ነገሮች የጻፋቸው ነገሮች ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ድርጊቱን በዓይናቸው ከተመለከቱ ከተለያዩ ሰዎች ጋር በመነጋገር የድርጊቶቹን እርግጠኝነት እንዳረጋገጠ ይገመታል፡፡

የከበርክ ቴዎፍሎስ

ሉቃስ ይህንን ያለው ለቴዎፍሎስ የነበረውን ክብርና አክብሮት ለማሳየት ፈልጎ ነው፡፡ ይህ ክፍል በባህላችሁ የተከበሩ ሰዎች የሚሰጣቸውን ስያሜ በመቀየር መጻፍ ይቻላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሰላምታን በመጠቀም “ለቴዎፍሎስ” ወይም “የተወደድክ ቴዎፍሎስ” ብለው መጻፍን ይመርጣሉ፡፡

የከበርክ

“የተከበርክ” ወይም “ክቡር”

ቴዎፍሎስ

የዚህ ሥም ትርጉም “የእግዚአብሔር ወዳጅ” ማለት ነው፡፡ ይህ ስም የዚህን ሰው ባሕርይ የሚገልጽ ስያሜ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ትክክለኛው የዚህ ሰው መጠሪያም ሊሆን ይችላል፡፡ በርካታ ትርጉሞች እንደ መጠርያ ስም አድርገው ተርጉመውታል፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)