am_tn/lev/26/37.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እስራኤላዊያን በጉልበት ወደ ጠላቶቻቸው አገር በሚሄዱበት ጊዜ ምን እንደሚሆን እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል

ከሰይፍ እንደሚትሸሹ

ሰይፍ የሚወክለው ሰይፍን በመያዝ ሊገድል የተዘጋጀ ሰው ወይም ከጠላት ሠራዊት የሚሆን ውጊያን ነው:: አት: “በሰይፍ ከሚያሳድዳችሁ እንደሚትሸሹ” ወይም “ከጠላት ሠራዊት እንደሚትሸሹ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)

በጠላቶቻቸው ፊት መቆም

በጠላቶች ፊት መቆምበጠላቶች ጥቃትና ውጊያ አለመውደቅን ያመለክታል:: አት: “በሚዋጉአችሁ ጊዜ ጠላቶቻችሁን ለመቋቋም” ወይም “ጠላቶቻችሁን መልሳችሁ ለመዋጋት” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)

የጠላቶቻችሁም ምድር ትቦጫጭቃችኋለች

እግዚአብሔር የጠላቶቻቸውን ምድር እስራኤላዊያንን እንደሚበላ እንደ አውሬ አድርጐ ይናገራል መቦጫጨቅ የሚለው ቃል አብዛኛዎቹ እስራኤላዊያን በዚያ እንደሚሞቱ ትኩረትን ይሰጣል አት በጠላቶቻችሁ ሀገር ትሞታላችሁ (See Personification/ አንድ ነገር አካል እንዳለው የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

ከእናንተ የተረፉት

ሳይሞቱ የቀሩት

በኃጢአታቸው መንምነው ያልቃሉ

በኃጢአታቸው መንመነው ማለቅ በኃጢአታቸው ምክንያት መንምነው ማለቅን ያመለክታል

የአባቶቻቸው ኃጢአት

እዚህ አባቶች የቀደሙ አባቶቻቸውን ያመለክታል (See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)