am_tn/lev/26/25.md

2.1 KiB

በላያችሁ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ

እዚህ “ሰይፍ” ሠራዊትን ወይም ከሠራዊት የሚደርስ ውጊያን ይወክላል:: አት: “የጠላት ሠራዊት አመጣበሃለሁ” ወይም “ጠላት እንዲዋጋህ አደርጋለሁ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)

እበቀላችኋለሁ

እቀጣችኋለሁ

ቃል ኪዳኔን ስላፈረሳችሁ

“ቃልኪዳኔን ስላልታዘዛችሁ” ወይም “ቃል ኪዳኔን ስለማትታዘዙ”

በሚትሰበሰቡበት ጊዜ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ትሰበሰባላችሁ” ወይም “ትሸሻላችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

ለጠላትም እጅ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ

እዚህ “እጅ” “ቁጥጥር ሥር” ማለት ሲሆን እናም በጠላት መሸነፍን ያመለክታል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ለጠላቶቻችሁ እጅ አሳልፊ እሠጣችኋለሁ” ወይም “ጠላቶቻችሁ እንዲቆጣጠራችሁ አደርጋለሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

የእንጀራችሁ እህል እንዲቋረጥ አደርጋለሁ

ሰዎች የሰበሰቡትን እህል ማጥፋት ወይም ሰዎች ይህን እንዳያገኙ ማድረግ የምግብ አቅርቦታቸውን ማቋረጥ ተደርጐ በተነግሮአል፡፡ አት፡ “የሰበሰባችሁትን እህል ባጠፋሁ ጊዜ” ወይም “ምግብን እንዳታገኙ ባደረግሁ ጊዜ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ላይ እንጀራ ይጋግራሉ

ይህም ጥቂት ዱቄት ከመኖር የተነሣ ብዙ ሴቶች የሚያመጡአቸው ለአንድ ምጣድ ብቻ እንደሚሆን ያመለክትል