am_tn/lev/26/21.md

2.1 KiB

በእኔ ላይ ማመጽ ቢትቀጥሉ

“መቀጠል” ባሕሪይን ይገልጻል:: በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ እግዚአብሔርን መቃወምን ወይም እርሱን አለመቀበልን ይወክላል አት: “በእኔ ላይ አታምጹ”

ሰባት እጥፍ መቅሠፍት እበትንባችኋለሁ

መበተን የሚለው ረቂቅ ስም መምታት በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: ሳባት ጊዜ እመታችኋለሁ:: (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

ሰባት እጥፍ መቅሠፍት እበትንባችኋለሁ

እግዚአብሔር በእስራኤላዊያን ላይ መቅሰፍትን ማምጣቱ በመቅሠፍት እንደሚመታቸው ወይም እንደሚጐዳቸው ተደርጐ ተገልጾአል አት: “በእናንተ ላይ ሰባት እጥፍ በላይ መቅሠፍት አመጣለሁ” ወይም “ሰባት ጊዜ በላይ በአሠቃቂነት እቀጣችኋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ሰባት እጥፍ

እዚህ ሰባት እጥፍ መደበኛ ሰባት ጊዜ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የቅጣቱን አሠቃቂነት ይጨምራል ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እንደ ኃጢአታችሁ መጠን

“ኃጢአቶች” የሚለው ረቂቅ ስም “ኃጢአት” በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ምን ያህል ኃጢአት እንደሠራችሁ በዚያ መጠን” (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)

ልጆቻችሁን ይነጥቁአችኋል

“መንጠቅ” ማለት ማጥቃት ወይም አስገድዶ ማውጣት ነው ::አት: “ልጆቻችሁን የነጥቁአችኋል” ወይም “ልጆቻችሁን አስገድደው ይወስዱባችኋል” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

መንገዶቻችሁም ሰው አልባ ይሆናሉ

“ማንም በመንገዶቻችሁ ላይ አይራመድም” አልባ ይሆናሉ ማለት ማንም በዚያ አይኖርም ማለት ነው