am_tn/lev/26/16.md

1.7 KiB

እነዚህን ነገሮች ቢያደርጉ

እነዚህ ነገሮች የሚለው ሀረግ በዘሌዋዊያን 26: 14-15 የተዘረዘሩ ነገሮችን ያመለክታል

የሚያስደነግጥ ትኩሳት አመጣባችኋለሁ

እዚህ ድንጋጤ እነርሱን ሊያስደነግጣቸው የሚችሉ ነገሮችን ያመለክታል:: አት: “የሚያስደነግጥ በሽታ አመጣባችኋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ሕይወታችሁን እንዲቀስፍ አሠቃያለሁ

ቀስ በቀስ ሕይወታችሁን እወስዳለሁ ወይም ቀሰ በቀስ እንዲትሞቱ አደርጋለሁ:: ይህንን የሚያደርጉት ትኩሳትና በሽታዎች ናቸው፡፡

የሚትዘሩት በከንቱ ነው

በከንቱ ነው የሚለው ሀረግ ከሥራቸው ምንም አያገኙም ማለት ነው፡፡ አት፡ “ዘርን በከንቱ ትዘራላችሁ” ወይም “ዘርን ትዘራላችሁ ነገርግን ከዚያ ምንም አታገኙም” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ፊቴን በእናንተ ላይ አከብድባችኋለሁ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር ለመጨከን እንደወሰነ ይናገራል:: አት: እናንተን ለመጥላት በሀሳቤ ወስኛለሁ:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በጠላቶቻችሁ ድል እንዲትሁኑ አደርጋለሁ

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ጠላቶቻችሁ ድል ያደርጓችኋል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)