ሃምሳኛ ዓመት
ይህ መደበኛ ቁጥር ነው፡፡ አት፡ 5ዐ ዓመት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ኢዩቤልዩ ይሁንላችሁ
ኢዩቤልዩ መሬትን ለርስቱ ባለቤት የሚመልሱበትና ለባሪያዎች ነጻነትን የሚያወጁበት ዓመት ነው
አት: “ምርኮ የመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የመመለስና ለባሪያዎች የነጻነት ዓመት”
ንብረትና ባሪያዎች ይመለሳሉ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ንብረትንና ባሪያዎችን መልሱ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)