am_tn/lev/24/19.md

2.4 KiB

አገናኝ ዐረፍተ ነገር

አንድ ሰው አንድን መጥፎ ነገር ቢያደርግ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል

የዚያው ዓይነት ጉዳት ይፈጸምበት

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የዚያው ዓይነት ጉዳት ፈጽሙበት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

በስብራት ፈንታ ስብራት በዐይን ፈንታ ዐይን በጥርስ ፈንታ ጥርስ

አነዚህ ሀረጐች አጽንዖት የሚሰጡት አንድ ሰው በሌላው ሰው ያደረሰበትን ጉዳት ተመሣሣይ ዓይነት ጉዳት በቅጣት እንዲቀበል ነው

በስብራት ፈንታ ስብራት

ይህ የተሠበሩ አጥንቶችን ያመለክታል:: አት: “በተሠበረው አጥንት ፈንታ የአጥንት ስብራት” ወይም “የአንድን ሰው አጥንት ሰብሮ እንደሆነ አጥንቱ ይሰበር” ወይም “የአንድን ሰው አጥንት ሠብሮ እንደሆን ከእርሱ አጥንቶች አንዱን ይስበሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

በዓይን ፈንታ ዓይን

ይህ ዓይን እንዲጐዳ ወይም እንዲወገድ ያመለክታል:: “የአንድን ሰው አይን አጥፍቶ እንደሆነ ከአይኖቹ አንዱ ይወገድ” ወይም “የአንድን ሰው አይን አጥፍቶ እንደሆነ ከእርሱ ዓይኖች አንዱን ያጥፉ” (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)

በጥርስ ፈንታ ጥርስ

ይህ የሚያመለክተው ጥርስን ከአገጭ መትቶ ማስወጣት ማለት ነው:: አት: “የአንድን ጥርስ አውልቆ ከሆነ ከጥርሶቹ አንድ ይውለቅ” ወይም “የአንድን ሰው ጥርስ አውልቆ ከሆነ ከጥርሶቹ አንዱን ያውልቁት” (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)

ማንም አንድን ሰው የሚገድል ይገደል

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሰውን የሚገድለውን ሰው ይግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)