አገናኝ ዐረፍተ ነገር
እግዚአብሔርን በረገመው ሰው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገር ቀጠለ
የራሱን በደል ይሸከማል
ስለኃጢአቱ የሚሠቃየው በደሉን እንደተሸከመ ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “ስለኃጢአቱ ይሠቀይ” ወይም “ይቀጣ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በእርግጥ ይገደል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሕዝቡ ይግደለው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)