am_tn/lev/24/03.md

1.5 KiB

አገናኝ ዐረፍተ ነገር

በመገናኛ ድንኳን ስላሉ ነገሮች እግዚአብሔር ለሙሴ መመሪያ መስጠቱን ይቀጥላል

ከምስክሩ መጋረጃ ውጭ በእግዚአብሔር ፊት

“የኪዳን ምሥክር” የሚለው ሀረግ ሕግጋት የተጻፉባቸው ጽላቶች ወይም ጽላቶች የተቀመጡበት ሣጥን ያመለክታል:: እነዚህም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተጀርባ ባለው እጅግ የተቀደሰ ቦታ በሆነው ክፍል ይቀመጣሉ፡፡ አት: “ከመጋጃው ውጭ በምስክሩ ጽላቶች ፊት” ወይም “ከመጋረጃው ውጭ በኪዳኑ ሣጥን ፊት” (See Synecdoche/ ክፍል ሙሉን እንደሚወክል እናም ሙሉ ክፍልን እንደሚወክል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)

መጋረጃው

በግድግዳ ላይ የሚንጠልጠል ወፍራም ጨርቅ ነው:: እንደመስኮት መጋረጃዎች ስስ አይደለም::

ከምሽት እስከ ጥዋት

“ከጸሐይ ጥልቀት እስከ ጸሐይ መውጣት” ወይም “ሌሊቱን ሙሉ”

ይህም ለሚመጡት ትውልዳችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው::

ይህም እነርሱ ሆነ ቀጣይ ትውልዳቸው ይህን ሥርዓት ለዘላለም መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 3:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::