am_tn/lev/20/17.md

2.8 KiB
Raw Permalink Blame History

አንድ ሰው ቢተኛ

ይህ አንድ ሰው ከእህቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙት መፈጸሙን ለዛ ባለ አባባል ይገልጻል:: አንዳንድ አባባሎች እንደ “አንድ ሰው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ” የሚሉ በጣም ቀጥተኛ ሀረጐችን ይጠቀማሉ:: (See Euphmism/ንኣብነት ወይም ለዛ ያለ ወይም በተዘዋዋሪነት አንድን ነገር ስለሚገልጹ ቃላት ይመልከቱ)

ከአባቱ ሴት ልጅ ወይም ከእናቱ ሴት ልጅ ጋር

ከተለየ አባት ወይም እናት ቢትሆንም ከእህቱ ጋር ግብረሥጋ ግንኙነት መፈጸም አይችልም የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ሙሉ እህት ወይም ግማሽ እህት ብትሆንም” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ተቆርጦ ይወገድ ወይም ተለይቶ ይጥፋ

ከማኀበረሰቡ የተገለለው ሰው ብጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ ተቆርጦ እንደተወገደ ተደረጐ ተገልጾአል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: ይህን ሃሳብ በዘልዋዊያን 7:2 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ አት፤ “ያ ሰው በሕዝቡ ዘንድ አይኑር” ወይም “ያን ሰው ከሕዝቡ ለዩት” (ዘይቤይዊ አነጋገር ወይም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)

በደሉን ይሸከማል

ይህ ሀረግ ሰውየው በኃጢአቱ ይጠየቅበታል ማለት ነው:: አት: “በኃጢአቱ ተጠያቂ ነው” ወይም “ቅጡት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

የወር አበባ ጊዜ

“ለአንድ ሴት በየወሩ ከማዕጸንዋ ደም የሚፈስስባት ጊዜ”

የፈሳሽዋን ምንጭ ገልጦአልና

በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋር ግንኙነት ማድረግን አንድ የተደበቀ ነገር ሽፋን መግለጥ ጋር ያነጻጽራል ይህ አሳፋሪ አድራጐት መሆኑ መገለጽ አለበት አት የደምዋን ፍሳሽ በመግለጡ አሳፋሪ ነገር አድርጐአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ግምታዊ አውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)

ሰውየውና ሴቲቱ ሁለቱም ተለይተው ይጥፉ

ይህ ለምን መደረግ እንዳበት በግልጽ ይነገር:: ይህን አሳፋሪ ተግባር ስለፈጸሙ ሰውየው ሴቲቱም ሁለቱ ተለይተው ይጥፉ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)