am_tn/lev/11/26.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::

ማንኛውም እንስሳ….በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን

ሕዝቡ አንዲመገቡ ያልተገቡ እግዚአብሔር የተናገራቸው እነዚህ እንስሳት በአካል ርኩስ ተብለው ተገልጸዋል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

ሰኰናው የተሰነጠቀ

አንድ ድፍን በመሆን ፈንታ ሰኰናው ለሁለት የተሰነጠቀ ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 11፡3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

የሚያመስኩ ወይም የሚያመነዥጉ

ይህ ምግብን ከሆድ እንደገና ወደ አፍ በማምጣት የሚያኝኩ እንስሳት ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 11፡3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡

እነዚህን የሚነካ ሰው ሁሉ ይረክሳል

እነዚህን እንስሳት በመንካቱ ምክንያት ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባ ሰው በአካል ርኩስ ተደርጐ ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)

መዳፍ

ሾህና ያላቸው እንስሳት መረገጫ አካል

እስከ ማታ

ጸሐይ እስክትጠልቅ