am_tn/lev/11/20.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::

ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ

“አስጸያፊ” የሚለው ቃል በግሥ ሃረግ ሊተረጐም ይችላል አት ክንፍ ኖሮአቸው አራት እግር ያሉአቸውን ነፍሳት ይጸየፉ፡፡ (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)

በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት

እዚህ “አራት እግር” የሚለው ሀረግ በምድር የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውንና እንደ አእዋፋት ከመሠሉ ሁለት እግር ካላቸው ከሚበርሩ ነፍሳት እንደሚለዩ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: አት፡ “በምድር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)

አንበጣ ፈንጣ ኩብኩባ

እነዚህ ዕጽዋት ተመጋቢና የሚፈናጠሩ ትናንሽ እንስሳት ናቸው፡፡ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)

ባለአራት እግር የሚበርሩ ፍጥረታት ወይም ነፍሳት

“አራት እግር ያሉአቸው የሚበርሩ ፍጥረታት”