am_tn/lev/10/14.md

1.7 KiB

የተወዘወዘውን ፍርምባና ለእግዚአብሔር የቀረበውን ወርች

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “ለእግዚአብሔር የተወዘወዘውና የቀረበው ፍርምባና ወርች” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ይመልከቱ)

ፍርምባ

ከአንገት በታች የሚገኝ የእንስሳ ፊት አካል ክፍል ነው፡፡

ወርች

ከጉልበት በላይ የሚገኝ ላይኛ የእግር አካል ክፍል ነው፡፡

ንጹህ በሆነ ሥፍራ

ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ጥቅም ተገቢ ሥፍራ በአካል ንጹህ ተብሎ ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)

እነዚህ ለእናንተ የተመደቡ ድርሻ ናቸው

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “እግዚአብሔር እነዚህን ለእናንተ ድርሻ አድርጐ ስጥቶአችኋል” (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ)

አንተ እና ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ

እዚህ “አንተ” አሮንን ያመለክታል:: (ሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)

ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል

ድርሻው ለአሮንና ለልጆቹ ተደርጐ እንደተገለጸ ይተርጉሙ፡፡ አት፡ “ይህ ድርሻ ሁልጊዜ ለአንተና ለልጆችህ ይሆናል” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)