am_tn/lev/07/28.md

2.4 KiB

ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው ለእስራኤላዊያን እንዲህ በላቸው መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው

ይህ በጥቅስ ውስጥ የተጠቀሰ ጥቅስ ነው፡፡ ቀጥተኛው ጥቅስ እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊወሰድ ይችላል፡፡ አት “ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን ተናገረ፤ እናም ለእስራኤል ሕዝብ እንዲናገር እንዲህ አለው፤ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው፤”(ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን መሥዋዕት በራሱ እጅ ያቅርበው

በራሱ እጅ ያቅርበው የሚለው አባባል በዐረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ሊቀመጥ ይችላል በእሳት ያቅርበው የሚለው ሀረግ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ፤ እርሱ ራሱ መሥዋዕት አድርጐ ለማቃጠል ያቀደውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርበው፤ (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ::)

በራሱ እጅ ያቅርበው

እዚህ “እጅ” መላውን ሰው ያመለክታል:: አት “እርሱ ራሱ ያቅርበው” (see synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ እናም ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤያዊ አነጋገር ወይም ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ)::

ፍርምባ

የአንድ እንስሳ ከአንገት በታች ፊተኛ የአካል ክፍል ነው

ፍርምባውን መሥዋዕት አድርጐ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዘው

ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ ካህኑ ይህን ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርጐ ሊያቀርብ ይችላል:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡

በእግዚአብሔር ፊት የሚወዘወዝ መሥዋዕት ተደርጐ ሊወዘወዝ ይችላል፤

መሥዋዕቱን ከፍ አድርጐ መያዝ ሰውየው መሥዋዕቱን ለእግዚአብሔር ማቅረቡ የሚያመለክት ምልክት ነው፡፡ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)::