am_tn/lam/05/19.md

1.7 KiB
Raw Permalink Blame History

አንተ ለዘላለም ትገዛለህ

ይሄ የሚያመላክተው ንግስናን እና መግዛትን ነው። “እንደ ንጉስ ግዛ ”

ከትውልድ እስከ ትውልድ

ዘይቤአዊ አገላለጽ ሲሆን። “ሁልግዜ” ለማለት ነው

ለምን ፈጽመህ ትረሳናለህ? ስለምንስ ለረዥም ጊዜ ትተወናለህ?

እግዚአብሔር እረስቶናል የሚለውን ሃሳብ ለማስተለለፍ ጸሓፊው ምልሽ የማይሰጠው ጥያቄን ይጠይቃል። በዓረፍተ ነገር መልኩም ሊጻፍ ይቻላል። “ለዘላለም ልትረሳን የመስላል፤ ተመለሰህም ለረጅም ግዜ ላትመጣ።”

ወደ አንተ መልሰን

”ወደራስህ መልሰን“

ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ

ዘመናችን የሚለው ሕይወታቸውን ነው። “ሕይወታችንን ቀድሞ እንደነበረው መልካም አድርገው” ወይንም “ቀድሞ ታላቅ እንደነበርነው ታላቅ አርገን”

ፈጽመህ ካልጣልኸን፣ ከመጠን በላይ ካልተቈጣኸን

ሊኖር የሚችለው ትርጉም፤ 1ጸሓፊው እግዚአብሔር አይመልሳቸው ዘንድ ተቆጥቶ እንዳይሆን ፈርቷል ወይንም 2 ጸሓፊው ማለት የፈለገው እግዚአብሔር እጅግ በጣም ስለተቆጣ አይመልሳቸውም

ከመጠን በላይ ካልተቈጣኸን

ይህ የሚያመላክተው የእግዚአብሔርን ሊለካ የማይችን የህል የተለቀ ቁጣ ነው። የማጋነን ዓይነት አገላለለፅ ነው። “እጅግ ተቆጣኧን”