am_tn/lam/05/05.md

1.1 KiB

አሳዳጆቻችን

“የሚያሳድዱን ጠላቶቻችን” ይሄ የሚያመላክተው ባቢሎናውያንን ነው።

ዕረፍትም የለንም

ይህ አባባል “ዕርፍትን” ተፈልጎ እንደሚገኝ ቁስ አድርጎ ይገልፀዋል። “ማረፍ አልቻልንም”

እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን

”ሰጠን“ የሚለው ዘይቤአዊ አገላለፅ ነው። “የምንበላውን እናገኝ ዘንድ ከአሦርና ከግብፅ ጋር ስምምነትን አደረግን” ወይንም “በሕይወት እንኖር ዘንድ እንድንበላ ዘንድ ለአሦርና ለግብፅ ተማርከናል”

የሉም

ይህ የሚያመላክተው መሞታቸውን ነው። “አለፉ” ወይንም “ሞተዋል”

እኛም በደላቸውን ተሸከምን

“በደል” የሚለው ከአባቶቻቸው ኋጥያት ምክንያት የመጣ ቅጣትን ያመላክታል። ”የኋጥያታቸውን ቅጣት ተሸክመናል“