am_tn/lam/04/09.md

1.6 KiB

በሰይፍ የሞቱ

“ሰይፍ” የሚለው የጠላታቸውን እነርሱን መውጋት ያመላክታል። በቀጥታ መልኩ “የጠላት ሰራዊት የገደላቸው” ሊባል ይችላል።

በራብ ከሞቱት

“ራብ” የሚያሳየው መራብን ነው። በቀጥታ መልኩ “በምግብ ማጣት የሞቱት” ሊባል ይችላል።

ደርቀው ያልቃሉ

“እጅግ በጣም የደረቁት እና የደከሙት”

እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል

“የምድርን ፍሬ” የሚለው ስለ ምግብ መብላት የሚናገር ነው። የምግብ ማጣት ሰዎችን እንደሚወጋ ሰይፍ ተደርጎ ነው የተገለፀው። “ይበሉ ዘንድ በቂ ምግብ ስላልነበረ ነው የሞቱት”

የርኅሩኆች ሴቶች እጆች

እዚህ ጋር ሴቶቹ “በእጆች” ነው የተመሰሉት። እጅግ ተርበው ስለነበረ ድሮ በመልካምነት ይታወቁ የነበሩት እና ለልጆቻቸው ርህራሄን ያደርጉ የነበሩት፤ አሁን ልጆቻቸውን ለምግብነት ቀቀሏቸው። “ርህሩህ ሴቶች” ወይንም “ከዚህ በፊት ርህሩህ ሆነው የሚያውቁ ሴቶች”

መብል ሆኑአቸው

“ልጆቻቸው ለሴቶቹ ምግብ ሆኑ”

የወገኔ ሴት ልጅ

ይህ ቅኔአዊ የእየሩሳሌም ስም አገላለፅ ሲሆን፣እዚህ ጋር በሴት ይመስላታል። “ሕዝቤ”