am_tn/lam/04/01.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ!

የእስራኤል ሕዝብን ማንፀባረቁን ባቆመ ወርቅ ይመስለዋል፣በዚህም ምክንያት ዋጋውን አጥቷል። “የእስራኤል ሕዝብ ማንፀባረቁን እንዳቆመ ወርቅ ነው፤ ውበቱን እንዳጣ ንጹህ ወርቅ ናቸው።”

ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ!

ይህ ጸሓፊው ነተፈጠረው ነገር እንዴት እንዳዘነ በአንክሮ ሲገልፅ ነው።

የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል

ቤተመቅደሱ በመፍረሱ የከበሩ ድንጋዮች በከተማው ተበትነዋል። የሰዎችንም መበተን የሚያሳይ ዘይቤአዊ አገላለጽ ሊሆ ን ይችላል።

በየመንገዱ ዳር

“መንገዶች በሚገጥምብቸው ቦታዎች በሙሉ” ወይንም “በ ሁሉም መንገዶች”

የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች

በከተማው ያሉ ሰዎች በከተማው ወንድ ልጆች ተመስለዋል። ሊኖሩትም የሚችሉት ትርጉም 1የእየሩስሌምን ወጣት ወንዶች ብቻ ማለቱ ነው ወይንም 2ሁሉንም በእየሩሳሌም ያሉ ሰዎች ለማለት ነው

የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣ እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ

ጸሓፊው የጽዮንን ልጆች ዋጋ ባጡ የሸክላ ዕቃዎች ይመስላቸዋል። “ሰዎች ዋጋ እንደሌላቸው የሸክላ ዕቃዎች ቆጠሯቸው”