am_tn/lam/03/58.md

1.9 KiB

ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ ሕይወቴንም ተቤዠህ

እግዚአብሔር በፍርድ ፊት እንዳይሞት እንደተሟገተለት፤ ጸሓፊው እግዚአብሔር ጠላቶቹ እንዳይገሉት እንዳደረገ ይናገራል። “ሕይወቴን ከጠላቶቼ አዳንካት። በፍርድ ፊት እንደተሟገትክልኝ ነው”

ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤

“ተሟገትክልኝ” የሚለው እርሱን ወክሎ እንደተከራከረለት ይናገራል። “ለእኔ ስትል ጉዳዬን ተከራከልክ”

ፍርዴን ፍረድልኝ

እዚህ ጋር እግዚአብሔር ጠበቃ መሆኑ ይቀርና ዳኛ ይሆናል። እግዚአብሔር ለእርሱ እንዲፈርድለት እየጠየቀ እንደሆነ ያስታውቃል። “ስለ እኔ ውሳኔን ወስን፤ እናም ትክክል እንደሆንኩኝ ለጠላቶቼ አስታውቅልኝ”

በቀላቸውን ሁሉ፣ በእኔም ላይ ያሰቡትን ዐድማ አየህ

“ስድባቸው” የሚለው ቃል እና ወይንም “ዕቅዳቸውን” የሚለው በድርጊታዊ ቃል ሊገለፅ ይችላል። “እንዴት እንደሰደቡኝ አይተሃል ምን ያህንም በእኔ ላይ እንደዶለቱ”

ስድባቸውን ሁሉ፣ በእኔ ላይ ያሰቡትን ዐድማ ሁሉ ሰማህ

“ስድባቸው” የሚለው ቃል “ፌዛቸው” ወይንም “ትንኮሳቸው” በሚለው ቃል ሊገለጽ ይችላል። ሊጎዱት ዕቅድ እንደነበራቸው በግልጽ ሊባል ይችላል። “እንዴ እንደተነኮሱኝ አይተሃል. . . ለእኔም የነበራቸውን ዕቅድ እንዲሁ” ወይንም “ሲያፌዙብኝ አይተሃል. . . ሊጎዱኝ ዕናቀዱብኝም እንዲሁ”