am_tn/lam/03/51.md

1.7 KiB
Raw Permalink Blame History

ማየቴ፣ ነፍሴን አስጨነቃት

ማየቴ የሚለው የሚወክለው የሚያየውን ነገር ነው። “የማየው ነገር ነፍሴን አስጨነቃት”

በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን

የከተማው ሴት ልጆች መከራን እየተቀበሉ መሆኑ ግልጽ ነው። “የከተማዬ ሴት ልጆ ች መከራን እየተቀበሉ ስለሆነ” ወይንም “የከተማዬ ሴት ልጆች መከራን ሲቀበሉ ስለማይ”

በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1የእየሩሳሌም ሴቶች ወይንም 2በእየሩሳሌም የሚኖሩ ሁሉ

ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣ እንደ ወፍ አደኑኝ

ጸሓፊው ሰዎች የሚያድኑትን እንስሳ ሉገድሉ እንደሚፈልጉ እርሱንም እንደ ሚፈልጉት ይናገራል። በቀጥታ መልኩ “የሚያድኑትን ወፍ እንደ ሚፈልጉ ጠላቶቼ ሊገድሉኝ ፈለጉኝ”

ሕይወቴን በጒድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ

“ወደ ጉድጓድ ወረወሩኝ” ወይንም “ወደ ጉድጓድ ጣሉኝ”

ድንጋይም በላዬ አደረጉ

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1“ወደ እኔ ድንጋይን ወረወሩ” ወይንም 2“ጉድጓዱን በድንጋይ ሸፈኑ”

ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ

“በጉድጓዱ ያለው ውሃ ከአናቴ በላይ ወጣ”

ጠፍቻለሁ ብዬ

“ጠፍቻለሁ” የሚለው መገደልን ይወክላል። በጣም ቶሎ መሞትን ያሳያል “ልሞት ነው”