am_tn/lam/03/44.md

1.7 KiB
Raw Permalink Blame History

ጸሎት እንዳያልፍ፣ ራስህን በደመና ሸፈንህ

ይሄ የሚያመላክተው እግዚአብሄር ላለመስማት እንደወሰነ ነው። “ጸሎታችንን አልሰማም አልክ፤ ጸሎታችንም አንተ ጋር እንዳይደርስ በዙሪያህ ደመናን ሸፈንክ”

በአሕዛብ መካከል አተላና ጥራጊ አደረግኸን

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1እግዚአብሔር እስራእኤላውያን በአሕዝብ ዘንድ ዋጋ ቢስ እንዲባሉ አደረክ። “አሕዛብ እንደ አተላ እና ቆሻሻ እንዲታሰቡ አደረክ” ወይንም 2) እግዚአብሔር ሕዝቡን በአሕዛብ መሃከል እንዲኖሩ ማድረጉ እንደ ቆሻሻ መጣል ነው። “እንደቆሻሻ በአሕዛብ መሃከል ጣልከን”

በችግርና በሽብር ተሠቃየን

“ችግር” እና “”ሽብር” ፥ “ጥፋት” እና “በመፈራረስ” የሚሉት በድርጊት መልኩ ሊገለፅ ይችላል። “እየተሸበርን ነው፤ ተጠምደናል እና እየፈረስን እና እየጠፋን ነው” ወይንም “ተሸብረናል ተጠምደናል። በአጠቃላይም ልንጠፋ ነው”

በችግር

ይሄ የሚያመላክተው ወደ ጉድጓድ መውደቅን ያመላክታል። በሁሉም መልኩ መጠመድን ያመላክታል።

በእኛ ላይ

“በእኛ ላይ የሆነው”

በጥፋትና በመፈራረስ፣

ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ቃላት ሲሆኑ፤ የእየሩሳሌምን መፍረስ ያመላክታሉ። “የሙሉ ለሙሉ ጥፋት”