am_tn/lam/03/40.md

1.4 KiB

ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ

“ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ” የሚለው የሚወክለው ለእርሱ መገዛትን ነው። “እንደገና ለእግዚአብሔር እንገዛ”

ልባችንን ከእጃችን ጋር . . . በሰማይ እናንሣ

“እጅን ወደ ሰማይ ከፍ ማድረግ” የሚያሳየው ከልብ መጸለይን ነው። ለእስራኤላውያን እጅን ወደላይ ከፍ አድርጎ መጸለይ ልማድ ነበረ። “እጃችንን ወደ ላይ ከፍ አድርገን ከልባችን እንጸልይ” ወይንም “ወደላይ ከፍ ባለ እጅ ከልባችን እንጸልይ”

ዐምፀናል፤ ኀጢአትም ሠርተናል

ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ቃላት ሲሆኑ፤ “ማመጽ” እና “ኋጥያት” መስራት ሁለቱም እግዚአብሔር ላይ ማመጽ እንደሆኑ ያሳያል።

ራስህን በቊጣ ከደንህ

እዚህ ጋር ቁጣን እግዚአብሔር የሚደርበው ልብስ አድርጎ ይናገረዋል። ብዙውን ግዜ በዕብራይስጥ ስሜት እንደ ልብስ ይገለፃል። “እጅግ በጣም ተናደሃል”

ገደልኸን

“ብዙዎቻችንን ገደልኧን”

ያለ ርኅራኄም

“ርኅራኄ” የሚለው የሚያሳየው ማዘንን ነው። “አላዘንክልንም”