am_tn/lam/03/30.md

1.5 KiB

ጒንጩን ለሚመታው ሰው ይስጥ

በውስጥ ታዋቂነት “እርሱ” የሚለው መከራን የሚቀበል ወይንም እግዚአብሔርን የሚጠባበቅ ማንንም ነው። “ጉንጩን ይስጥ” የሚለው የሚወክለው ሰው ጉንጩን እንዲመታ መስጠትን ነው። “ፊቱን እንዲመቱት ለሰዎች ይፍቀድ”

ውርደትንም ይጥገብ

ጸሓፊው የሚናገረው በውስጡ እንደ ውሃ ውርደትን ሊሞላ እንደሚችል ዕቃ ነው። በውርደት መሞላት ማለት በጣም መዋረድ ማለት ነው። ማስተላለፍ የፈለገው በዚህ ግዜ መታገስ እንዳለበት ነው። “ብዙ ይዘለፍ” ወይንም “ሰዎች ሲያዋርዱት ይታገስ”

መከራን ቢያመጣ እንኳ

“እግዚአብሔር ሰዎች መከራ እንዲደርስባቸው በያረግም” ወይንም “ሰዎችን ቢቀጣም”

ይራራል

“በእነርሱ ላይ ርህራሄ ይኖረዋል”

ሆን ብሎ ችግርን፣ ወይም መከራን አያመጣምና

“ሆን ብሎ” የሚለው ፍላጎትን እና እርካታን ያመላክታል፤ “በሰዎች ላይ መከራን በማምጣት ደስ አይለውም” ወይንም “ሰዎችን በመቅጣት እርካታን አያገኝም”

በሰው ልጆች ላይ

ይሄ በአጠቃላይ ስለ ሰዎች ይናገራል። “ሰዎች” “የሰው ልጆች”