1.4 KiB
1.4 KiB
እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት
ሊኖረው የሚችለው ትርጉም:1)“በእሩሱ ላይ የሚደገፉ ሁሉ” ወይንም 2)“እርሱ የሆነ ነገርን እስከሚያደርግ ድረስ የሚጠብቅ”
ለሚፈልገውም ሰው
“መፈለግ” የሚለው ሊኖረው የሚችለው ትርጉም:1)እግዚአብሔርን ዕርዳታ መጠየቅ 2)እግዚአብሔርን ለማወቅ መፈለግ
በወጣትነቱ ቀንበር ቢሸከም
ቀንበር የሚለው የሚያመላክተው መከራን ነው። “በወጣትነት” የሚለው ልጅነትን ያመላክታል። “በልጅነት ግዜው የደረሰበት መከራ
ብቻውን ዝም ብሎ ይቀመጥ
“ዝም ብሎ” የሚለው አለመናገርን ያመላክታል። እዚህ ጋር አለማጉረምረምን ለማለት ነው። “ያለመናገር በቻውን ይቀመጥ” ወይንም “ሳያጉረመርም ብቻውን ይቀመጥ”
አሸክሞታልና
“ቀንበሩ ሲጫንበት” ቀንበር የሚለው የሚያመላክተው መከራን ነው። “መከራን ሲቀበል”
ፊቱን በዐቧራ ውስጥ ይቅበር
ፊትን በዐቧራ መቅበር አንገትን ወደ ምድር ማቀርቀርን ያመላክታል። “እዛው ፊቱን ወደ መሬት አዘቅዝቆ ይቆይ”